ዐቃቤ ሕግ ደረጃ ሦስት

Position: Full Time

Organization: FDRE Ministry of Justice

Not Specified

ኢፌዲሪ የፍትሕ ሚኒስቴር በሕግ የተጣለበትን ኃላፊነት በላቀ ለመወጣት ይችል ዘንድ የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ በማውጣት የአሰራር እና የአደረጃጀት ማሻሻያዎችን አድርጓል። በአዲሱ አደረጃጀት መሠረት ለህዝብ ግንኙነት እና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ተመድበው ለመስራት ፍላጎቱ እና ተነሳሽነቱ ያላቸው እና ከዚህ በታች የተመላከቱ መስፈርቶችን የሚያሟሉ የሕግ ባለሙያዎችን በዐቃቤ ሕግነት ለመቅጠር ይህ ማስታወቂያ ወጥቷል። በመሆኑምይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 30 ቀናት ውስጥ በተወዳዳሪነት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን።

አስፈላጊ የሆኑ መስፈርቶች፡

ኢትዮጵያዊ የሆነ/የሆነች እና በኢትዮጵያ የሚኖር /የምትኖር ፤ ለሕገ መንግስቱ እና ለሕግ የበላይነት ተገዢ የሆነ/የሆነች ፤ የየትኛውም የፖለቲካ ድርጅት አባል ያልሆነያልሆነች ፤ በታታሪነቱ/ቷ ፣ በታማኝነቱ/ቷ ፣ በሥነ-ምግባሩ/ሯ መልካም ስም ያተረፈች መሆኑን⁄ኗን ይማርበት/ ትማርበት ከነበረበት ዩኒቨርሲቲ ወይም ከሚኖሩበት አካባቢ ካለ የመንግስት ተቋም ማስረጃ ማቅረብ የሚችል /የምትችል፤ የወንጀል ቅጣት ሪከርድ የሌለበት/ባት ፤ የፌዴራል መንግስቱን የሥራ ቋንቋ የሚችል/የምትችል ፤ እንደ አስፈላጊነቱ የሚሰጠውን የጽሁፍም ይሁን የቃል ወይም ሁለቱንም ፈተና መውሰድ እና ማለፍ የሚችል /የምትችል፤ የሥራ መደብ፡ ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፡

የስራ መስፈርቶች

የትምህርት ደረጃ፡

  • ከከፍተኛ ትምህርት ተቋም በሕግ ትምህርት በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቀ /የተመረቀች

  • በ 2016 ዓ.ም ወይም 2017 ዓ.ም የተመረቀ /የተመረቀች እና የመመረቂያ ነጥብ (Cumulative GPA) ለወንድ 3.5፣ ለሴት 3.25 እና ለአካል ጉዳተኛ ወንድ 3.25 ሴት 3.00 እና ከዚያ በላይ ያለው /ያላት

  • የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ውጤት 85 ፐርሰንታይል እና ከዛ በላይ በማምጣት ፈተናውን ያለፈ/ያለፈች

የስራ ልምድ፡

  • በህዝብ ግንኙነት እና ኮሚዩኒኬሽን 1(አንድ ዓመት) እና ከዚያ በላይ የሰራ/የሰራች

ብዛት: 2

የማመልከቻ መመሪያ

አመልካቾች የሚከተለውን ሊንክ በመጫን ማመልከት ይችላሉ፡ THIS LINK

ማስታወሻ፡ አመልካቾች ለምዝገባ ስትመጡ ኢትዮጵያዊ መሆናችሁን የሚገልጽ መታወቂያ/ፓስፖርት እና ብሔራዊ መታወቂያ በpdf ስካን የተደረገ፤ ይሰሩበት ከነበረው መስሪያ ቤት የተጻፈ የሥራ ልምድ እና የሥነ-ምግባር ማስረጃ በpdf ስካን የተደረገ እና ዋና የትምህርት ማስረጃ (student copy) ጨምሮ በpdf ስካን የተደረገ ይዛችሁ መምጣት ይኖርባችኋል፡፡

ለበለጠ መረጃ፡ በስራ ሠዓት በስልክ ቁጥራችን ፡- +25115157432 በመደወል፤ እንዲሁም በኢሜል አድራሻችን፡- mojprosecutorsadministration@justice.gov.et ላይ በመፃፍ ማግኘት ይችላሉ።

Deadline: Nov 3, 2026, 12:00 AM

Location:

Amount: Not Specified