የሰው ኃይል አስተዳደር ባለሙያ
Position:
Organization: Eco Real Estate
Not Specified
የሥራው መግለጫ
የሰው ኃይል አስተዳደር ባለሙያው በድርጅታችን ሥር ባሉና በከፍተኛ ፍጥነት እያደጉ ባሉ የሪል እስቴት፣ የካፌ እና የሬስቶራንት ዘርፎች ውስጥ ያሉትን አጠቃላይ የሰው ኃይል ተግባራት በበላይነት ይቆጣጠራል። የሥራ መደቡ ባለቤትም የሰው ኃይል ምልመላና ቅጥርን ማካሄድን፣ ሥልጠናዎችን ማመቻቸትን፣ የሠራተኞች ግንኙነትን ማጠናከርን፣ የአፈጻጸም ግምገማዎችን መምራትን፣ እንዲሁም ለእያንዳንዱ ዘርፍ ተስማሚ የሆኑ የሥራ መግለጫዎችንና የደረጃ ዕድገት ሥርዓቶችን መቅረጽን ያጠቃልላል። በተጨማሪም የሠራተኞች ስንብት፣ ፈቃድና እረፍት ጊዜያትን ጨምሮ ማናቸውም የሰው ኃይል ውሳኔዎች ከኢትዮጵያ የአሠሪና ሠራተኛ ሕግጋት ጋር የተጣጣሙ መሆናቸውን በማረጋገጥ፣ የድርጅታችንን የልህቀትና የእድገት ራዕይ በንቃት ይደግፋል።
የስራ መስፈርቶች
የትምህርት ደረጃ፡
በሰው ኃይል አስተዳደር፣ በቢዝነስ አስተዳደር ወይም በተመሳሳይ የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው/ያላት
የስራ ልምድ፡
ቢያንስ ከ2-5 ዓመታት በሰው ኃይል አስተዳደር የስራ ልምድ ያለው/ላት
በሪል እስቴት ወይም በግንባታ ዘርፍ ላይ የሰራ/ች ቢሆን ይመረጣል
ዋና ዋና ኃላፊነቶች
ቅጥር እና የሠራተኛ ኃይል
የስራ ቅጥር ማስታወቂያዎችን ማዘጋጀት እና መለጠፍ እንዲሁም ማስተዳደር
ለሽያጭ፣ ለገበያ፣ ለግንባታ እና ለአስተዳደር ሚናዎች እጩዎችን ማጣራት፣ ቃለ መጠይቅ ማድረግ፣ መገምገም እና ውጤቱን ማሳወቅ
የሰራተኞችን የስራ አፈፃፀምን መገምገም እና ደረጃ መስጠት
ስንበቶችን እና እርፍትን ከሐገሪቱ አሰሪ እና ሰራተኛ ሐጎች ጋር መጣጣማቸውን ማረጋገጥ
የስራ ውል እና የስራ መግለጫ ማዘጋጀት
ዋስትናዎች መገምገም እና መሟላታቸውን ማረጋገጥ
የሠራተኞች ግንኙነት
ለሠራተኞች ስጋቶች እና ለግጭት አፈታት የመጀመሪያ የመገናኛ ነጥብ ሆኖ ማገልገል
ከድርጅቱ እሴቶች ጋር የተጣጣመ አዎንታዊ የሥራ ቦታ ባህል ማጎልበት
የቡድን ግንባታ እና የስልጠና ክፍለ ጊዜዎችን ማደራጀት
የአፈጻጸም አስተዳደር
ለሽያጭ ወኪሎች፣ ለሽያጭ ሱፐርቫይዘሮች እና ለቢሮ ሰራተኞች የግምገማ ስርዓቶችን እና KPIዎችን መተግበር
ውጤታማነትን ለማሻሻል ስልጠና እና ግብረመልስ መስጠት
መረጃ እና ሰነድ አያያዝ
የኢትዮጵያን የሠራተኛ ሕጎች፣ ኮንትራቶች እና የሰው ኃይል ፖሊሲዎች ማክበርን
ትክክለኛ የሠራተኛ መዝገቦችን (ኮንትራቶች፣ የእረፍት ጊዜ፣ ጥቅማ ጥቅሞች) በአግባቡ መያዝ
የድርጅቱን የሰው ኃይል አሠራር ሕጋዊነት ለማረጋገጥ ከመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ጋር ጠንካራ የሥራ ትስስር መፍጠርና መያዝ
ስልጠናዎች
የክህሎት ክፍተቶችን በመለየት በሽያጭ ቴክኒኮች፣ በደንበኛ አገልግሎት እና በግንባታ ደህንነት ላይ ስልጠናዎችን ማዘጋጀት
ለሠራተኞች የሙያ መሻሻያ ፕሮግራሞችን መደገፍ
ካሳ እና ጥቅማ ጥቅሞች
የደመወዝ ክፍያ፣ ጥቅማ ጥቅሞች ማጥናት እና ደረጃዎቸን መመደብ
ክህሎቶች
ስለ ኢትዮጵያ የሠራተኛ ሕግ እና የሰው ኃይል ምርጥ ልምዶች ጠንካራ እውቀት ያለው/ያላት
በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ እጅግ በጣም ጥሩ የመግባቢያ ክህሎቶች
በሰው ኃይል አስተዳደር ሶፍትዌር እና በማይክሮሶፍት ኦፊስ ብቃት ያለው/ያላት
ጠንካራ የአደረጃጀት እና የብዙ ሥራ ክህሎቶች
በፍጥነት በሚሄድ የሪል እስቴት አካባቢ ውስጥ ጫናዎችን ተቋቁሞ የመሥራት ብቃት
ከፍተኛ ታማኝነት እና ምስጢር ጠባቂነት
የማመልከቻ መመሪያ
ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አመልካቾች የትምህርት እና የስራ ልምድ ማስረጃችሁን በኢሜል አድራሻችን ecorealestate@gmail.com ወይም ቦሌ አትላስ ትራፊክ መብራት ወረድ ብሎ ኖህ ሴንትረም አፓርትመንት ጎን ካለው ኢኮ ሪል እስቴት አትላስ ሪቨር ሳይድ ሳይት ህንፃ 3ኛ ፎቅ በአካል በመምጣት ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን +251973555550 /+251973555551 ይደውሉ፡፡
Job Requirements በሰው ኃይል አስተዳደር፣ በቢዝነስ አስተዳደር ወይም በተመሳሳይ የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው/ያላት አግባብነት ካለው የስራ ልምድ ጋር ዋና ዋና ኃላፊነቶች - ለሽያጭ፣ ለገበያ፣ ለግንባታ እና ለአስተዳደር ሚናዎች እጩዎችን ማጣራት፣ ቃለ መጠይቅ ማድረግ፣ መገምገም እና ውጤቱን ማሳወቅ - የስራ ቅጥር ማስታወቂያዎችን ማዘጋጀት እና መለጠፍ እንዲሁም ማስተዳደር - ለሠራተኞች ስጋቶች እና ለግጭት አፈታት የመጀመሪያ የመገናኛ ነጥብ ሆኖ ማገልገል - የቡድን ግንባታ እና የስልጠና ክፍለ ጊዜዎችን ማደራጀት - ትክክለኛ የሠራተኛ መዝገቦችን (ኮንትራቶች፣ የእረፍት ጊዜ፣ ጥቅማ ጥቅሞች) በአግባቡ መያዝ - የክህሎት ክፍተቶችን በመለየት በሽያጭ ቴክኒኮች፣ በደንበኛ አገልግሎት እና በግንባታ ደህንነት ላይ ስልጠናዎችን ማዘጋጀት - ለሠራተኞች የሙያ መሻሻያ ፕሮግራሞችን መደገፍ - የደመወዝ ክፍያ፣ ጥቅማ ጥቅሞች ማጥናት እና ደረጃዎቸን መመደብ How to Apply ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አመልካቾች የትምህርት እና የስራ ልምድ ማስረጃችሁን በኢሜል አድራሻችን ecorealestate@gmail.com ወይም ቦሌ አትላስ ትራፊክ መብራት ወረድ ብሎ ኖህ ሴንትረም አፓርትመንት ጎን ካለው ኢኮ ሪል እስቴት አትላስ ሪቨር ሳይድ ሳይት ህንፃ 3ኛ ፎቅ በአካል በመምጣት ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን +251973555550 /+251973555551 ይደውሉ፡፡Deadline: Jul 24, 2026, 12:00 AM
Location:
Amount: 1
