Assistant Auto Electrician

Position:

Organization: CTG Human Resources and Logistics Plc

Not Specified

የስራ መስፈርቶች

  • የትምህርት ደረጃ፡ ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በአውቶ ኤሌክትሪሲቲ በደረጃ I/II/III/IV የተመረቀ

  • የሥራ ልምድ፦ በመስኩ ውስጥ በመንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች (NGOs) ወይም በተባበሩት መንግስታት (UN) ኤጀንሲዎች ቢያንስ 3 (ሦስት) ዓመት የሥራ ልምድ ወይም በንግድ ድርጅት 5 (አምስት) ዓመት እና ከዛ በላይ ተዛማጅ የሥራ ልምድ ያለው (የቀላልና የከባድ ተሽከርካሪዎች የመስክ ሥራ ልምድን ያጠቃልላል)

  • ብዛት፡ 20

  • ደመወዝ፡ በድርጅቱ ስኬል መሰረት

  • የስራ ቦታ ፦ ሀዋሳ፣ ጅግጅጋ፣ ጎዴ፣ ድሬደዋ፣ መቀሌ፣ ጎንደር፣ ጋምቤላ እና ኮምቦልቻ

  • ተፈላጊ የትምህርት ማስረጃ፦ ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በአውቶ (Auto Electricity) የተመረቀ።

ዋና ዋና ኃላፊነቶች

  • የላቁ የኮምፒውተር የቴክኒክ ምርመራ እና መመርመሪያ (Diagnostic) ዘዴዎችን በመጠቀም የማንኛውንም ተሽከርካሪ ወይም መሣሪያ ሁኔታ ለመንገድ ብቁ መሆኑን ወይም ደህንነቱን መመርመር፣ ማረጋገጥ እና የተሟላ ሪፖርት ማቅረብ

  • በተሽከርካሪ/መሣሪያ አምራቹ በተቀመጠው መደበኛ የሥራ ጊዜ ገደብ ውስጥ አስፈላጊ የሆኑ መሣሪያዎችን እና ቁሳቁሶችን በመጠቀም ተሽከርካሪዎችን፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎችን ወይም አካላትን በአስተማማኝ ሁኔታ መጠገን፣ መንከባከብ፣ ማስተካከል ወይም ማደስ

  • የተከናወኑ ሥራዎች ሁሉ የተቀመጡትን አነስተኛ መስፈርቶች ማሟላታቸውን ለማረጋገጥ የቴክኒክ አገልግሎት መረጃዎችን እና ሕጋዊ የጥገና ደረጃዎችን መተርጎም እና መተግበር

  • እንደ አልተርኔተር ፣ ስታርተር ሞተር ያሉ የኤሌክትሪክ አካላትን ለተሽከርካሪዎችም ሆነ ለኤሌክትሪክ ጄነሬተር ኃይል ሰጪ ክፍሎች (240 ቮልት) ሙሉ ጥገና (Overhaul) ማድረግ

  • የኤሌክትሪክ ጥገና አሰራሮችን እና ደረጃዎችን በተመለከተ የድርጅቱን መመሪያዎች ሙሉ በሙሉ መተግበራቸውን ማረጋገጥ፤ በዚህም የመሣሪያዎችን ዝግጁነት ማሳደግ እና ወጪን መቀነስ

  • በተሽከርካሪዎች፣ በአካላት ወይም በስርዓቶች ላይ የተከሰቱ ብልሽቶችን መንስኤ ለማወቅ ተገቢውን የብልሽት መመርመሪያ ዘዴዎች በደረጃ እና በምክንያታዊነት መተግበር፤ እንዲሁም ደህንነትንና አስተማማኝነትን ለማሻሻል የሚረዱ የለውጥ የውሳኔ ሃሳቦችን ማቅረብ

  • ሁልጊዜም አስተማማኝ የሥራ ልምዶችን እና የአሰራር ሂደቶችን መጠቀም፣ እንዲሁም የድርጅቱን የጤና እና ደህንነት ፖሊሲ ማክበር ይህም የመከላከያ አልባሳትን መልበስ እና ለአካባቢ ጥበቃ ትኩረት መስጠት

ክህሎቶች

  • በከባድ የጭነት መኪናዎችና በተሽከርካሪዎች ወርክሾፕ ውስጥ በአውቶ ኤሌክትሪካል ሲስተም ጥገና፣ አገልግሎትና አጠባበቅ ላይ ተግባራዊና በቂ ልምድ ያለው

  • የአማርኛ ቋንቋን የመናገር፣ የማንበብና የመጻፍ በጣም ጥሩ ችሎታ ያለው

  • ከዋናው አውቶ ኤሌክትሪሻን ጋር በመተባበር ለቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎች፣ ለተሳቢዎች (Trailers) እና ለማሽነሪዎች የኤሌክትሪክ ጥገና ሥራዎችን በአምራቹ መመዘኛ መሠረት በብቃት ማከናወን የሚችል

  • የተበላሹ ወይም የቆሙ ተሽከርካሪዎችንና መሣሪያዎችን ተገቢ ቴክኒኮችን በመጠቀም ለሕዝብ አደጋ በማይፈጥር መልኩ ማንሳትና ማጓጓዝ የሚችል

  • የድርጅቱን የሥራ ቦታ ጤናና ደህንነት (Health & Safety) ፖሊሲዎችና መመዘኛዎች አክብሮ፣ የግል መከላከያ መሣሪያዎችን (PPE) በመጠቀም ለመሥራት ፈቃደኛ የሆነ

  • በኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ የሥራ ቦታዎች ተመድቦ ለመሥራትና አልፎ አልፎ የመስክ ጉዞዎችን (Field Missions) ለማድረግ ፈቃደኛ የሆነ

የማመልከቻ መመሪያ

ከዚህ በላይ የተቀመጠውን መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች የሕይወት ታሪካችሁን (CV)፣ የማይመለስ የትምህርትና የሥራ ልምድ ማስረጃችሁን ኮፒ እና የማመልከቻ ደብዳቤ (Cover Letter) በኢሜል አድራሻችን ctgethiopia@ctg.org መላክ ትችላላችሁ።

ማስታወሻ፡ አመልካቾች በኢሜሉ ርዕስ (subject line) ላይ የስራ መደቡን መጠሪያ "ረዳት አውቶ ኤሌክትሪሻን " እና መስራት የሚፈልጉበትን ከተማ በመጥቀስ ማመልከት ይኖርባቸዋል፡፡

Job Requirements ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በአውቶ ኤሌክትሪሲቲ በደረጃ I/II/III/IV የተመረቀ አግባብነት ካለው የስራ ልምድ ጋር ዋና ዋና ኃላፊነቶች - የላቁ የኮምፒውተር የቴክኒክ ምርመራ እና መመርመሪያ (Diagnostic) ዘዴዎችን በመጠቀም የማንኛውንም ተሽከርካሪ ወይም መሣሪያ ሁኔታ ለመንገድ ብቁ መሆኑን ወይም ደህንነቱን መመርመር፣ ማረጋገጥ እና የተሟላ ሪፖርት ማቅረብ - በተሽከርካሪ/መሣሪያ አምራቹ በተቀመጠው መደበኛ የሥራ ጊዜ ገደብ ውስጥ አስፈላጊ የሆኑ መሣሪያዎችን እና ቁሳቁሶችን በመጠቀም ተሽከርካሪዎችን፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎችን ወይም አካላትን በአስተማማኝ ሁኔታ መጠገን፣ መንከባከብ፣ ማስተካከል ወይም ማደስ - የተከናወኑ ሥራዎች ሁሉ የተቀመጡትን አነስተኛ መስፈርቶች ማሟላታቸውን ለማረጋገጥ የቴክኒክ አገልግሎት መረጃዎችን እና ሕጋዊ የጥገና ደረጃዎችን መተርጎም እና መተግበር - እንደ አልተርኔተር ፣ ስታርተር ሞተር ያሉ የኤሌክትሪክ አካላትን ለተሽከርካሪዎችም ሆነ ለኤሌክትሪክ ጄነሬተር ኃይል ሰጪ ክፍሎች (240 ቮልት) ሙሉ ጥገና (Overhaul) ማድረግ - የኤሌክትሪክ ጥገና አሰራሮችን እና ደረጃዎችን በተመለከተ የድርጅቱን መመሪያዎች ሙሉ በሙሉ መተግበራቸውን ማረጋገጥ፤ በዚህም የመሣሪያዎችን ዝግጁነት ማሳደግ እና ወጪን መቀነስ How to Apply ከዚህ በላይ የተቀመጠውን መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች የሕይወት ታሪካችሁን (CV)፣ የማይመለስ የትምህርትና የሥራ ልምድ ማስረጃችሁን ኮፒ እና የማመልከቻ ደብዳቤ (Cover Letter) በኢሜል አድራሻችን ctgethiopia@ctg.org መላክ ትችላላችሁ። ማስታወሻ፡ አመልካቾች በኢሜሉ ርዕስ (subject line) ላይ የስራ መደቡን መጠሪያ "ረዳት አውቶ ኤሌክትሪሻን " እና መስራት የሚፈልጉበትን ከተማ በመጥቀስ ማመልከት ይኖርባቸዋል፡፡

Deadline: Oct 19, 2026, 12:00 AM

Location:

Amount: 20