School Workflow & Operational Advisor

Position:

Organization: Askuala Link Trading PLC

Not Specified

የሥራው መግለጫ

በአስኳላ ሊንክ ትምህርት ቤቶች የእለት ተእለት ስራቸውን እንዲያቃልሉ እና የትምህርት ቤት አስተዳደር አሰራርን ዘመናዊ ለማድረግ እንሰራለን። ያዘጋጀናቸው የቴክኖሎጂ መፍትሔዎች ከትምህርት ቤቶች ነባራዊ ሁኔታ እና ከክፍል ውስጥ እውነተኛ የሥራ ሂደት ጋር በትክክል መጣጣማቸውን ለማረጋገጥ፣ የዘርፉን ተሞክሮ ያካበቱ በትምህርት ቤት አስተዳደር፣ በዕለት ተዕለት የሥራ ሂደቶች እና በስራ አመራር ዙሪያ ተግባራዊ ልምድ እና ሀሳብ የሚያካፍሉን ልምድ ያላቸው ባለሙያዎችን እንፈልጋለን።

የስራ መስፈርቶች

የትምህርት ደረጃ፡

  • በማንኛውም የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ዲግሪ እና ከዛ በላይ ያለው/ላት

የስራ ልምድ፡

  • 2 ዓመት

  • በአሁኑ ወቅት በግል ትምህርት ቤት ውስጥ ስራ አስኪያጅ/አስተዳዳሪ፣ ምክትል ስራ አስኪያጅ ወይም የIT መምህር ሆነው በመስራት ላይ ያለ/ለች

ብዛት፡ 1

የሥራ ቦታ፡ ባሉበት የሚሠራ (ከማንኛውም የኢትዮጵያ ክፍል ማመልከት ይቻላል)

የቅጥር ሁኔታ፡ በትርፍ ጊዜ

ደመወዝ፡ በድርጅቱ ስኬል መሠረት

ዋና ዋና ኃላፊነቶች

  • የትምህርት ቤት የአሰራር ሂደቶችን በመመርመር የተሻሻሉ መንገዶችን ማቅረብ

  • የአሰራር ስርዓቶችን ማቀናጀት እና የተሻለ የስራ ብቃት እንዲኖር መደገፍ

  • የትምህርት ቤቱን የአስተዳደር እና የክፍል አሰራር ሂደቶች መገምገም

  • ችግሮችን መለየትና ተግባራዊ የመፍትሄ ሀሳቦችን ማቅረብ

  • የአሰራር መመሪያዎችን፣ የስራ ሂደት ሰነዶችን እና የማሻሻያ ሀሳቦችን ማዘጋጀት

  • ከአስተዳደር፣ መምህራን እና ሰራተኞች ጋር በመተባበር የተቀላጠፈ አሰራር ማረጋገጥ

  • የትምህርት ቤቶች የስራ ቅልጥፍና፣ ጥራት እና ውጤታማነት እንዲሻሻል ተገቢውን እገዛ ማድረግ

  • የስራ አፈጻጸም ሪፖርቶችን ማዘጋጀትና ለሚመለከተው የስራ ክፍል ማቅረብ

ክህሎት

  • ስለ ግል ትምህርት ቤቶች የውስጥ አሰራር፣ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ እና የአስተዳደር መዋቅር ጥልቅ ግንዛቤ ያለው/ላት

የማመልከቻ መመሪያ

አመልክት/ቺ የሚለውን ይጫኑ

ማስታወሻ፡ አመልካቾች ሙሉ ስም፣ በትምህርት ቤቱ ውስጥ ያለዎት ወቅታዊ የሥራ መደብ (ለምሳሌ፡ አስተዳዳሪ፣ ምክትል አስተዳዳሪ፣ ወይም የIT መምህር)፣ የትምህርት ቤቱ ስም፣ የትምህርት ቤቱ ደረጃ/ዓይነት (ለምሳሌ፡ መዋዕለ ሕፃናት፣ የመጀመሪያ ደረጃ፣ ሁለተኛ ደረጃ፣ ወይም ከቅድመ-መደበኛ እስከ 12ኛ ክፍል)፣ የትምህርት ቤቱ አድራሻ (ክልል፣ ከተማ፣ እና ክፍለ ከተማ/ወረዳ) እና ስልክ ቁጥር በመጥቀስ ማመልከት ሲኖርባቸው ሙሉ መረጃ የሌላቸው ማመልከቻዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም። የተመረጡ አመልካቾች ብቻ ለቃለ-መጠይቅ ይጠራሉ።

Job Requirements በማንኛውም የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ዲግሪ እና ከዛ በላይ ያለው/ላት አግባብነት ካለው የስራ ልምድ ጋር ዋና ዋና ኃላፊነቶች - የትምህርት ቤት የአሰራር ሂደቶችን በመመርመር የተሻሻሉ መንገዶችን ማቅረብ - የአሰራር ስርዓቶችን ማቀናጀት እና የተሻለ የስራ ብቃት እንዲኖር መደገፍ - የትምህርት ቤቱን የአስተዳደር እና የክፍል አሰራር ሂደቶች መገምገም - ችግሮችን መለየትና ተግባራዊ የመፍትሄ ሀሳቦችን ማቅረብ - የአሰራር መመሪያዎችን፣ የስራ ሂደት ሰነዶችን እና የማሻሻያ ሀሳቦችን ማዘጋጀት - ከአስተዳደር፣ መምህራን እና ሰራተኞች ጋር በመተባበር የተቀላጠፈ አሰራር ማረጋገጥ - የትምህርት ቤቶች የስራ ቅልጥፍና፣ ጥራት እና ውጤታማነት እንዲሻሻል ተገቢውን እገዛ ማድረግ - የስራ አፈጻጸም ሪፖርቶችን ማዘጋጀትና ለሚመለከተው የስራ ክፍል ማቅረብ How to Apply አመልክት/ቺ የሚለውን ይጫኑ ማስታወሻ፡ አመልካቾች በአሁኑ ወቅት በግል ትምህርት ቤት ውስጥ ስራ አስኪያጅ/አስተዳዳሪ፣ ምክትል ስራ አስኪያጅ ወይም የአይቲ መምህር ሆነው በመስራት ላይ ያሉ መሆን ሲኖርባቸው ሙሉ ስም፣ በትምህርት ቤቱ ውስጥ ያላቸው ወቅታዊ የሥራ መደብ( ስራ አስኪያጅ/አስተዳዳሪ፣ ምክትል ስራ አስኪያጅ ወይም የአይቲ መምህር) ፣ የትምህርት ቤቱ ስም፣ የትምህርት ቤቱ ደረጃ/ዓይነት (ለምሳሌ፡ መዋዕለ ሕፃናት፣ የመጀመሪያ ደረጃ፣ ሁለተኛ ደረጃ፣ ወይም ከቅድመ-መደበኛ እስከ 12ኛ ክፍል)፣ የትምህርት ቤቱ አድራሻ (ክልል፣ ከተማ፣ እና ክፍለ ከተማ/ወረዳ) እና ስልክ ቁጥር በመጥቀስ ማመልከት ይኖርባቸዋል፡፡

Deadline: Jul 30, 2026, 12:00 AM

Location:

Amount: 1