Position:
Organization: SNFD Bakery PLC
የፋይናንስ ቡድናችንን ለመቀላቀል ዝርዝር ተኮር፣ ልምድ ያለው ከፍተኛ አካውንታንት እንፈልጋለን። በጣም ጥሩው እጩ የእለት ተእለት የሂሳብ ስራዎችን የመቆጣጠር፣ የፋይናንስ ሪፖርት አቀራረብን ትክክለኛነት የማረጋገጥ እና የበጀት እና የኦዲት ስራዎችን የመደገፍ ሃላፊነት አለበት። ይህ ሚና ጠንካራ የትንታኔ ክህሎቶችን, የሂሳብ መርሆዎችን ጥልቅ ዕውቀት እና አነስተኛ ሰራተኞችን የመምራት እና የመምራት ችሎታን ይጠይቃል.
ብዛት፡ 5
ከሠራተኛም ሆነ ከደንበኞች ተሰብስቦ ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ገቢ የሚደረጉ የሥራ ግብር ፤ ጡረታ ፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎችም ወቅቱን ጠብቆ ዝርዝሩን በማዘጋጀት እንዲከፈል ለፋይናንስ ክፍል ማቅረብ እና እንዲከፈል ክትትል ማድረግ ፤
ከሠራተኞች ከደመወዝ ጋር ተያይዞ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ተገቢና አፋጣኝ ምላሽ መስጠት
በየወሩ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሪፖርት ከመደረጉ በፊት ወርሃዊ የእጅ በእጅ እና የዱቤ ሽያጭ ደረሠኞች አባሪዎች ከሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ ወርሃዊ ዜድ ሪፖርት ጋር በማመሳከር ከሽያጭ መመዝገቢያ ውጭ የተከናወኑ ሽያጮችን ዝርዝር በማጣመር ማጠቃለያ ሪፖርት ማዘጋጀት ፤
በኮንትራት የሚደረጉ ክፍያዎች በስምምነቱ እና በግዢ መመሪያ መሠረት መሆኑን ማረጋገጥ ፤
የድርጅቱ ሂሳብ በውጭ ሂሳብ አጣሪዎች በሚመረመርበት ጊዜ አስፈላጊዎቹን ሰነዶችና መረጃዎች ያቀርባል፣ ያስተባብራል፣ በስቶር የሚያዙትን ስቶክ ካርኮች በየጊዜው ያስታርቃል፤
የድርጅቱን ቋሚ ንብረቶች በቋሚ ንብረት መዝገብ ላይ ይመዘግባል፣ የእያንዳንዱን ቋሚ ንብረት የእርጅና ቅናሽ በመመሪያው መሠረት በማስላት ይመዘግባል
የደመወዝና የትርፍ ሰዓት ወጭዎችን በደመወዝ መክፈያ ሊስት መሠረት ቀጥተኛ ያልሆነ ወጭን ለይቶ በሂሳብ አርዕስትና በየወጭ ማዕከል (Cost Center)ይመዘግባ፣ እያንዳንዱ ሥራ የፈጀውን የጉልበት ሰዓት በተፈቀደው መጠን (Rate) በማባዛት በጆብ ካርድ ላይ ይመዘግባል፤
የትምህርት ደረጃ፡ የመጀመርያ ዲግሪ ወይም ዲፕሎማ በአካውንቲንግ ወይም በተመሳሳይ የትምህርት መስክ የተመረቀ/ች
የስራ ልምድ፡ 5 አመት በአምራች ኢንዱስትሪ ላይ የስራ/ች ቢሆን ይመረጣል
አመልካቾች ዋናውን የትምህርት እና የስራ ልምድ ማስረጃ ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር በመያዝ አባሃዋ መ/ቤት አጠገብ በሚገኘው ሙልሙል ዳቦ ፋብሪካ/ ወይም 22 አካባቢ ድንበሯ ሆስፒታል አጠገብ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ወይም በኢሜል mulmulhr@gmail.com ማመልከት ይችላሉ።
ለበለጠ መረጃ +251114624401 መደወል ይችላሉ።
Deadline: Jun 5, 2025, 12:00 AM
Location: Hayahulet
Amount: 5