Videographer

Position:

Organization: Super SGS Trading

Not Specified

ድርጅታችን የሚሰራው በዲጂታል ማርኬቲንግ/ሶሻል ሚዲያ ማርኬቲንግ እና ማማከር ነው፡፡

Online መተግበሪያን በማጎልበት እና ድርጅታዊ ስልጠናዎችን ጨምሮ ሰፊ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን በ LMSፕላትፎረም ትምህርቶችን ኮርሶችን ይሰጣል፡፡ ስለዚህ ለዚሁ ስራ በቪዲዮ ከፕሪ እስከ ፖስት ድረስ መስራት የሚችል ማድረግ የሚችል ባለሙያ በዚህ ላይ በቂ እውቀት እና ልምድ ያለው ከፍተኛ ተነሳሽነት እየፈለግን ነው።

የደንበኞቻችን ፍላጎት ተከትሎ ቪዲዮ መቅረጽ፣ ማስተካከል (ኤዲት ማድረግ) የሚችል የቪዲዮግራፊ ባለሙያ እንፈልጋለን፡፡ የቪዲዮግራፈሩ ሚና ለስራው የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች መሟላታቸውን መከታተል፣ የካሜራ ባለሙያዎችን መምራት፣ እና ቪዲዮዎችን ኤዲት ማድረግ የሚችል ሊሆን ይገባዋል፡፡

በቪዲዮ ግራፊ ሙያ ስኬታማ ለመሆን ባለሙያው የደንበኞችን ፍላጎት በጥሞና አዳምጦ የሚረዳና ፈጠራ የታከለበት ክህሎት አስተባብሮ የሚጠበቀውን ውጤት ማስረከብ የሚችል ሊሆን ይገባዋል፡፡ ጎበዝ የቪዲዮ ግራፊ ባለሙያ የስራውን ጥራት የሚጨምሩ ዘመኑ ያፈራቸውን ገበያው የሚፈልጋቸውን አዳዲስ አሰራሮች፣ አቀራረቦችን እየተከታተለ በየጊዜው ራሱን የሚበቃ ሊሆን ይገባዋል፡፡ 

ደሞዝ: 12000

ብዛት፡ 2

የቪዲዮ ግራፈሩ ኃላፊነቶች:

  • በተገቢው ቦታ የቪዲዮ እና የፎቶ ምስሎች መቅረጽ

  • በየጊዜው የስራ መሳሪያዎቹን ዝግጁነት መገምገምና ማሟላት

  • ከስራ ባልደረቦችና ከደንበኞች ጋር ሆኖ የስራ እቅድ ማርቀቅ

  • ከቀረጻ በኋላ የቪዲዮ ምስሎን ማረም (ቪዲዮ ኤዲቲንግ ማከናወን)

  • ተፈላጊው የቪዲዮ ምስል በተገቢ ሆኑታ እንዲቀረጽ ሌሎችን የቪዲዮግራፊ ባለሙያዎች ማስተባበር

የስራ መስፈርቶች፡

  • የትምህርት ደረጃ፡ በተመሳሳይ የትምህርት ዘርፍ የተመረቀ/ች

  • ከፕሪ እስከ ፖስት ፕሮዳክሽን መስራት የሚችል/ምትችል፡፡

  • የስራ ልምድ፡ 3 አመት የስራ ልምድ

ተፈላጊ ልዩ ችሎታዎች:

  • ከፍተኛ የሆነ የኮምፒውተር አጠቃቀም ችሎታ

  • የኦንላይን እና ኦፍለይን ሶፍትዎሮችን መጠቀም የሚችል

  • ከፍተኛ የሆነ የአዶቤ ፎቶሾፕ አጠቃቀም ችሎታ

  • አስደናቂ የካሜራ አጠቃቀም ችሎታ

የማመልከቻ መመርያ:

  • ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አመልካቾች የስራ ልምድዎን እና ማንኛውም ተዛማጅ ደጋፊ ሰነዶችን በቴሌግራም ይህን ሊንክ በመጠቀም ማመልከት ይችላሉ።

  • ለበለጠ መረጃ፡ +251908222223 ወይም +251914 949494

  • አድራሻ፡ ከመካኒሳ ወደጀርመን በሚወስደው መንገድ ላይ የኪራይ ቤቶች ህንጻ ላይ 2ኛ ፎቅ

Job Requirements Educational background in a realted field of study with relevant work experience, able to work from pre- to post-production. Responsibilities of the Videographer: - Capture video and photo images in appropriate locations - Regularly review and replenish the readiness of work equipment - Develop a work plan with colleagues and clients - Edit the video image after recording (perform video editing) - Coordinate other videographers to ensure that the required video image is captured properly Required Special Skills: - Excellent computer skills - Proficient in using online and offline software - Excellent Adobe Photoshop skills - Excellent camera skills How to Apply ከታች ያለውን ሊንክ በመጠቀም ያመልክቱ። ለበለጠ መረጃ፡ +251908222223 ወይም +251914 949494 አድራሻ፡ ከመካኒሳ ወደጀርመን በሚወስደው መንገድ ላይ የኪራይ ቤቶች ህንጻ ላይ 2ኛ ፎቅ

Deadline: Jun 7, 2025, 12:00 AM

Location:

Amount: 2

SIMILAR JOBS

No results found

feeling blue