Position:
Organization: Super SGS Trading
ድርጅታችን የሚሰራው በዲጂታል ማርኬቲንግ/ሶሻል ሚዲያ ማርኬቲንግ እና ማማከር ነው፡፡
Online መተግበሪያን በማጎልበት እና ድርጅታዊ ስልጠናዎችን ጨምሮ ሰፊ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን በ LMSፕላትፎረም ትምህርቶችን ኮርሶችን ይሰጣል፡፡ ስለዚህ ለዚሁ ስራ በቪዲዮ ከፕሪ እስከ ፖስት ድረስ መስራት የሚችል ማድረግ የሚችል ባለሙያ በዚህ ላይ በቂ እውቀት እና ልምድ ያለው ከፍተኛ ተነሳሽነት እየፈለግን ነው።
የደንበኞቻችን ፍላጎት ተከትሎ ቪዲዮ መቅረጽ፣ ማስተካከል (ኤዲት ማድረግ) የሚችል የቪዲዮግራፊ ባለሙያ እንፈልጋለን፡፡ የቪዲዮግራፈሩ ሚና ለስራው የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች መሟላታቸውን መከታተል፣ የካሜራ ባለሙያዎችን መምራት፣ እና ቪዲዮዎችን ኤዲት ማድረግ የሚችል ሊሆን ይገባዋል፡፡
በቪዲዮ ግራፊ ሙያ ስኬታማ ለመሆን ባለሙያው የደንበኞችን ፍላጎት በጥሞና አዳምጦ የሚረዳና ፈጠራ የታከለበት ክህሎት አስተባብሮ የሚጠበቀውን ውጤት ማስረከብ የሚችል ሊሆን ይገባዋል፡፡ ጎበዝ የቪዲዮ ግራፊ ባለሙያ የስራውን ጥራት የሚጨምሩ ዘመኑ ያፈራቸውን ገበያው የሚፈልጋቸውን አዳዲስ አሰራሮች፣ አቀራረቦችን እየተከታተለ በየጊዜው ራሱን የሚበቃ ሊሆን ይገባዋል፡፡
ደሞዝ: 12000
ብዛት፡ 2
በተገቢው ቦታ የቪዲዮ እና የፎቶ ምስሎች መቅረጽ
በየጊዜው የስራ መሳሪያዎቹን ዝግጁነት መገምገምና ማሟላት
ከስራ ባልደረቦችና ከደንበኞች ጋር ሆኖ የስራ እቅድ ማርቀቅ
ከቀረጻ በኋላ የቪዲዮ ምስሎን ማረም (ቪዲዮ ኤዲቲንግ ማከናወን)
ተፈላጊው የቪዲዮ ምስል በተገቢ ሆኑታ እንዲቀረጽ ሌሎችን የቪዲዮግራፊ ባለሙያዎች ማስተባበር
የትምህርት ደረጃ፡ በተመሳሳይ የትምህርት ዘርፍ የተመረቀ/ች
የሰራ ልምድ፡ 2 አመት የስራ ልምድ
ከፍተኛ የሆነ የኮምፒውተር አጠቃቀም ችሎታ
የኦንላይን እና ኦፍለይን ሶፍትዎሮችን መጠቀም የሚችል
ከፍተኛ የሆነ የአዶቤ ፎቶሾፕ አጠቃቀም ችሎታ
አስደናቂ የካሜራ አጠቃቀም ችሎታ
አመልካቾች በሃሁጆብስ ፕራይመሪ https://hahu.jobs/ ወይም በቴሌግራም ቦት https://t.me/hahujobs_bot የሃሁጆብስ ፕሮፋይላችሁን በማያያዝ ማመልከት ትችላላችሁ።
Deadline: May 31, 2025, 12:00 AM
Location:
Amount: 2